ስቴቨን ሀውኪንግ የ76 አመቱ የአለማችን ታላቅ ሳይንቲስት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል

ስቴቨን ሀውኪንግ የ76 አመቱ የአለማችን ታላቅ ሳይንቲስት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል

በፊዚክሱ አለም በህዋ ሳይንስ በዘመናችን በርካታ ስራዎችን አበርክቷል። ሰባት መፅሀፍቶቹ በሚሊየን በሚቆጠር ኮፒዎች ተሽጠዋል።

የአካል ጉዳተኛና የአእምሮ ነርቭ በሽታ ተጠቂ ሲሆን መናገርም ሆነ መራመድ አይችልም።

ምንም ያህል ህይወት አስቸጋሪ ብትመስልም፣ ሁሌም ማድረግና ማሳካት የምትችለው የሆነ ነገር ግን አለ፣ ዋናው ነገር እጅ አለመስጠትህ ነው” የሚለው ስቴቨን መናገር አለመቻሉን በኮምፒውተር ታግዞ ከሰዎች ጋር መግባባት ችሏል፣ ይህንን እንደ ጉድለት ሳይመለከት

ዝምተኛ ሰዎች የሚጮህ አእምሮ ባለቤት ናቸው” ይላል። በ21 አመቱ ወንበር ላይ ሲውል ዶክተሮች ጥቂት ጊዜ እንደሚቆይ ቢናገሩም እሱ ግን 55 አመታትን ተሻግሮ በ76 አመቱ ሞቷል።

ቀና ብለህ ከዋክብትን እንጅ አጎንብሰህ እግርህን አትመልከት፣ በስራህ ላይ እጅ አትስጥ፣ ስራ ለህይወትህ ትርጉምና አላማ ይሰጠዋል….. ” ይላል።

ፕሮፌሰሩ ስቴቨን ሀውኪንግ አካል ጉዳተኝነት አካልን ሳይሆን የአእምሮ ብርታትን ብቻ ለሚጠይቀው ሳይንስ የተመቸ እንደሆነ ያስባል።

የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሆኖ ህይወቱ በልዩ ልዩ ግኝቶችና ሽልማቶች የደመቀለት ይህ ሰው ለብዙዎቻችን ህይወት ምሳሌ መሆን ይችላል።

አልችልም በሚል ምክንያት በህይወታችን ውስጥ የተሻለ ነገርን ማበርከት፣ አዲስ ነገርን ማስገኘት፣ የበኩላችንን መወጣት ስንችል እምቢ ብለን ከቤት እየዋልን አለፍ ሲልም በሱሰኝነት ውስጥ ራሳችንን ደብቀን ምንም ትርጉም

ሳይኖረን ለምንሄድ ሰዎች የስቴቨን አይነት ሰዎች ስለምን መኖር እንዳለብን እንድንጠይቅ ያደርጉናል።

ህይወት አንድ እድል ብቻ ናት፣ ይች እድል ድጋሜ አትገኝም በቃ ያለፉት የሚመኙት የወደፊቶቹ የሚያገኙት እኛ እየኖርንበት ያለነው ብቸኛ እድል ነው፣ ስለዚህም እንጠቀምበት እላለሁ!!! መልካም ቀን!