ከወደ ህንድ ሰሞኑን የተሰማው ወሬም አንድ ሰው በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ሆኖ የመዳን ተስፋ ከሌለውና አሟሟቱን ማሳመር ከፈለገ ሊፈቀድለት ይገባል

ኪዳኔ መካሻ (የህግ ባለሞያ በድሬቲዩብ)

ከወደ ህንድ ሰሞኑን የተሰማው ወሬም አንድ ሰው በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ሆኖ የመዳን ተስፋ ከሌለውና አሟሟቱን ማሳመር ከፈለገ ሊፈቀድለት ይገባል የሚል ነው። ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይህን የወሰነው የሰው ልጅ በክፋ ደዌ መኖር ስቃይ ከሆነበት በህክምና እርዳታ እንዲሞት ሊፈቀድለት ይገባል ብሎ ነው።

ይህን ውሳኔ የሰሙ ሁለት የ88 እና የ78 አመት የቦምቤይ አረጋውያን ጥንዶችም፤ እሰየው ውሳኔውን እኛም ስንናፍቀው ነበር ብለዋል።