ከሰዎች መጠበቅ የሌሉብን አንዳንድ ነገሮች

1በሀሳባችን እንዲስማሙ መጠበቅ የለብንም እኛ ወደዚህች ምድር የመጣነው ሌሎች ሰዎች በሚጠብቁን ልክ ለመኖር አይደለም። የራሳችን ስኬት ማረጋገጫዎችም ሌሎች ሰዎች ሳይሆኑ ራሳችን መሆን ይገባናል።

ስለዚህ ለማናቸውም ሀሳቦቻችን ከሌሎች ሰዎች የ “ይለፍ” ፍቃድ መጠበቅ የለብንም። ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ጋርም ማነጻጸር አይጠበቅብንም።

2, ሰዎች ከመጠን በላይ እንዲያከብሩን መጠበቅ የለብንም … ማንም ሰው ራሳችንን ከምናከብረው በላይ ሊያከብረን አይችልም። ራሳችን ለራሳችን መስጠት የምንችለውን ፍቅር፣ ክብር እና ትኩረት ከማንም ሰው መለመን ወይም መጠበቅ የለብንም። ራሳችንን መውደድና ማክበር ስንጀምር ደስተኛ መሆን

እንጀምራለን።

3, የምናስበውን እንዲያውቁ መጠበቅ የለብንም … ሰዎች እኛ ምን እያሰብን እንደሆነ እንዲያውቁ መጠበቅ የለብንም። ሰዎች ህሊናን ማንበብ አይይቸሉም፤ ካልተነገራቸው በስተቀር ምን እንደሚሰማን በትክክል ለመረዳት ይከብዳቸዋል። ሰለዚህ አንደበታችንን ከፍተን ራሳችንን በደንብ ግልጽ ማድረግ ይኖርብናል

4 ዘሰዎች በፍጥነት እንዲለወጡ መጠበቅ የለብንም ሰዎችን መለወጥ አለብን ብለን አጨናንቀናቸው ከአጠገባችን እንዲርቁ ከምናደርግ ራሳቸውን የሚመለከቱበት እድል እና ሰፊ ጊዜ ብንሰጣቸው የተሻለ ነው።