የታክሲ አሽከርካሪው ማርቆስ ዘሪሁን በአዲስ አባባ ጎዳና ነፍሰ ጡር ሴትን ያላአንዳች ክፍያ ያደርሳል

የታክሲ አሽከርካሪው ማርቆስ ዘሪሁን በአዲስ አባባ ጎዳና ነፍሰ ጡር ሴት ስታጋጥመው ወደ ምርመራ ተቋም አሊያም ወደ ምትሄድበት ቦታ ያላአንዳች ክፍያ ያደርሳታል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅም ለዚህ ለመልካም ሰው የዓለም የጤናማ እናትነት ወር ምክንያት በማድረግ የእውቅና የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል፡፡

እስቲ እናንተም በመንገድ ስታገኙት ስለበጎው ስራው አመስግኑት፡አበረታቱት፡፡