ቡሬ ሜሪ ጫኔ በሚል የሴት ስም በዘረፋ የተሰማራ ወጠምሻ ተያዘ

ምእራብ ጎጃም ከወደቡሬ የተሰማው ዜና ደግሞ አንዲህ ነው።

በምስሉ ላይ የምታዮት መልከ መልካም ቆንጆ በቡሬ ከተማ አስተዳደር የሀሰት ማስረጃ በመያዝ ሜሪ ጫኔ በሚል የሴት ስም በመያዝና የጉሃ ጺዎን ከተማ የፍልቅልቅ ቀበሌ ነዋሪ መታወቂያ በመያዝ ፆታውን በመቀየር የሴት ልብስ በመልበስ ወንዶችን በማማለልና የተማረከውን ወንድ በማታ ሊስማት ሲጠጋ

ጉዳት በማድረስ በዘረፋ ወንጀል ተሰማርታ ቆይታለች።

ይህቺን ሴት በቀን 8/ 7/2010 ዓ.ም የቡሬ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏታል።

ቀሚሷም ሲወልቅ ወጠምሻ ጎረምሳ ሆኖ ተገኝቷል።

በእንደዚህ አይነት ወንጀል እንዳትሸወዱ ተጠንቀቁ !!!

/source-የቡሬ ከተማ ኮሙኒኬሽን/